የአጠቃቀም ውሎች

የአጠቃቀም ደንብ እና ሁኔታ 

ዕትም፡ 2.1 | መጨረሻ የተሻሻለው፡ ሰኔ 05/2018 .

ይህ የአጠቃቀም ውል ("ውል") የethioCall የሞባይል መተግበሪያን እና በቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ሚድል ኢስት ኤፍ.ዜ.ኢ ("ethioCall"፣ "እኛ"፣ "እኛን" ወይም "የእኛ") የሚቀርቡ ተዛማጅ አገልግሎቶችን የእርስዎን መዳረሻ እና አጠቃቀም ይገዛል። መተግበሪያውን በማውረድ፣ በመድረስ ወይም በመጠቀም፣ በዚህ ውል ለመገዛት ተስማምተዋል።

በዚህ ውል ካልተስማሙ፣ መተግበሪያውን መጠቀም ወዲያውኑ ማቆም አለብዎት።

1. ስለ አገልግሎቱ

ethioCall ዓለም አቀፍ የጥሪ አገልግሎቶችን፣ የቅድመ-ክፍያ ዕቅዶችን እና ተዛማጅ የቴሌኮሙኒኬሽን ባህሪያትን ያቀርባል። መተግበሪያው የአደጋ ጊዜ ጥሪ ተግባራትን አይሰጥም።

2. ብቁነት

አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅብዎታል፡

•   ዕድሜዎ ቢያንስ 13 ዓመት፣ ወይም በእርስዎ የሕግ ክልል ውስጥ በዲጂታል ስምምነት ሕግ የተደነገገው ዕድሜ መሆን፤

•   በአገርዎ ውስጥ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ለመጠቀም በሕግ የተፈቀደልዎት መሆን።

•   መተግበሪያውን በመጠቀም፣ እነዚህን የብቁነት መስፈርቶች ማሟላትዎን ያረጋግጣሉ።

3. የአካውንት ምዝገባ

አብዛኛዎቹን የአገልግሎቶች ይዘቶች ለመጠቀም የሞባይል ስልክ ቁጥርዎን በመጠቀም አካውንት መመዝገብ አለብዎት።

አገልግሎቶቹን በመጠቀምዎ የሚከተሉትን ለማድረግ መስማማትዎን አረጋግጠዋል ማለት ነው፡፡

•   ትክክለኛ እና የተሟላ መረጃ ማቅረብ፤

•   የአካውንትዎን ምስጢራዊነት መጠበቅ፤

•   በአካውንትዎ ስር ለሚከናወኑ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ኃላፊ መሆን።

ማንኛውም የምዝገባ መረጃ ሐሰተኛ፣ ያልተሟላ ወይም አሳሳች ሆኖ ከተገኘ፣ አካውንትዎን ልናግድ ወይም ልናቋርጥ እንችላለን።

4. ተቀባይነት ያለው አጠቃቀም ፖሊሲ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ ethioCallን ለማንኛውም ሕገ-ወጥ፣ ጎጂ ወይም አግባብ ያልሆነ ዓላማ መጠቀም አይችሉም፡፡

•   ማጭበርበር፣ ማታለል ወይም በሌላ ሰው መምሰል፤

•   ትንኮሳ ወይም ዛቻ፤

•   ስፓሚንግ (spamming) ወይም በብዛት መደወል፤

•   የቴሌኮሙኒኬሽን ቁጥጥር ደንቦችን መጣስ፤

•   መተግበሪያውን መመልሶ መስራት (ሪቨርስ ኢንጂነር ማድረግ)፣ ማሻሻል ወይም ማስተጓጎል መሞከር፤

•   አውቶማቲክ ሲስተሞችን ወይም ቦቶችን (bots) መጠቀም፤

•   በኔትወርክ ወይም በአገልግሎት ስራ ላይ ጣልቃ መግባት።

ይህንን ፖሊሲ መጣስ አካውንትዎ ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል።

5. የቴሌኮሙኒኬሽን ገደቦች

•   ethioCall የእርስዎ የሞባይል ኦፕሬተር ምትክ አይደለም።

•   በethioCall የአደጋ ጊዜ ጥሪዎችን (ለምሳሌ 911፣ 999፣ 112) ማድረግ አይችሉንም፡፡

•   የጥሪ ጥራት በእርስዎ መሣሪያ፣ በኢንተርኔት ግንኙነት እና በሶስተኛ ወገን አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ሊመሰረት ይችላል።

በአገር ውስጥ ሕጎች፣ በቴሌኮም ደንቦች፣ በአገልግሎት ሰጪዎች ገደቦች ወይም በመንግሥት መስፈርቶች ምክንያት የአገልግሎቶች መገኘት እንደ አገር ወይም ክልል ሊለያይ ይችላል።

ተጠቃሚዎች የethioCall አጠቃቀማቸው ተፈጻሚነት ካላቸው የአገር ውስጥ ሕጎች እና ደንቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።

6. ግዢዎች እና ክፍያዎች

6.1 በመተግበሪያ ውስጥ የሚፈጸሙ ግዢዎች

በመተግበሪያው ውስጥ ያሉ ሁሉም ግዢዎች በሚከተሉት በኩል ይከናወናሉ፡

•   አፕል ስቶር ቢሊንግ

•   ጉግል ፕሌይ ቢልንግ

የእርስዎን የክፍያ ካርድ መረጃ አናከማችም ወይም አናቀናብርም (ፕሮሰስ አናደርግም)።

6.2 ተመላሽ የመደረግ ገንዘብ (ክፍያ)

ሁሉም የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄዎች በሚመለከተው የመተግበሪያ መደብር (አፕል አፕ ስቶር ወይም ጎግል ፕሌይ) በኩል መቅረብ አለባቸው። የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄን በቀጥታ በራሳችን አናስተናግድም፡፡

6.3 ዋጋ አወጣጥ

የዕቅዶች እና የክሬዲቶች ዋጋዎች በመተግበሪያው ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፣ እንደ ክልል፣ ታክስ ወይም ምንዛሬ ሊለያዩ ይችላሉ።

7. የጥሪ ክሬዲቶች እና ዕቅዶች

•   የጥሪ ክሬዲቶች እና ዕቅዶች የግል ናቸው እና ለሌላ ሰው ሊተላለፉ አይችሉም።

•   የጥሪ ክሬዲቶች och ዕቅዶች ጥቅም ላይ የሚውሉ የዲጂታል ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች ሲሆኑ፣ ጥሪው ሲገናኝ ወይም አገልግሎቱ ሲነቃ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

•   የጥሪ ክሬዲቶች በአገልግሎት አጠቃቀም ጊዜ የሚውሉ በመሆናቸው በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም። የገንዘብ ተመላሾች፣ አግባብነት ባለው ቦታ፣ በአፕል አፕ ስቶር (Apple App Store) ወይም በጎግል ፕሌይ (Google Play) ፖሊሲዎች መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናል።

•   የጥሪ ክሬዲቶች በመተግበሪያው ውስጥ ከተጠቀሰው የጸናበት ጊዜ (validity period) በላይ ካልተጠቀሙባቸው ጊዜያቸው ሊያበቃ ይችላል።

•   የጥሪ ዕቅዶችን በአግባቡ አለመጠቀም ወይም ያልተለመዱ የአጠቃቀም ዘይቤዎች አገልግሎቱን ማገድ ወይም ማቋረጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ቨርቹዋል ቁጥሮች

•   በሚገኝበት ቦታ፣ አገልግሎቱ ለተጠቃሚዎች ቨርቹዋል የስልክ ቁጥሮችን ሊሰጥ ይችላል።

•   ቨርቹዋል የስልክ ቁጥሮች የአገልግሎት አቅራቢው ንብረት ሆነው የሚቀጥሉ ሲሆን፣ ከስራ ማስኬጃ፣ ከቁጥጥር ወይም ከቴሌኮሙኒኬሽን መስፈርቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ በድጋሚ ሊመደቡ፣ ሊነሱ፣ ሊታገዱ ወይም ሊቀየሩ ይችላሉ።

•   ቨርቹዋል ቁጥርን የማግኘት መብት በመተግበሪያው ውስጥ በተጠቀሰው መሠረት ገቢር የሆነ ዕቅድ ወይም የደንበኝነት ምዝገባን በመንከባከብ ላይ ሊመሰረት ይችላል።

8. የአገልግሎት አቅርቦት

ምን ጊዜም ቢሆን አስተማማኝ አገልግሎትን ለመስጠት ጥረት የምናድርግ ሲሆን ነገር ግን ለሚከሉት ሁኔታዎች ዋስትና የማንሰጥ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

•   ያልተቋረጠ አቅርቦት፤

•   ከስህተት የጸዳ አሠራር፤

•   ይህ ነው ተብሎ የተቀመጠ የጥሪ ጥራት።

የአገልግሎት መአቅርቦት በኢንተርኔት መቋረጥ፣ በአገልግሎት ሰጪዎች ገደቦች፣ በመንግሥት እገዳዎች፣ ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ወይም በሶስተኛ ወገን መሠረተ ልማት ብልሽቶች (እክሎች) ምክንያት ሊስተጓጎል ይችላ ሊነካ ይችላል።

በቅድሚያ ማሳሰቢያ (ማስታወቂያ) መስጠት ሳይጠበቅብን ማናቸውንም የአገልግሎት አይነት ልንቀይር፣ ልናግድ ወይም ልናቆም እንችላለን።

9. አካውንት ማቋረጥ

እርስዎ የሚከተሉትን ካደረጉ አካውንትዎን ልናቋርጥ ወይም ልናግድ እንችላለን፡

•   ይህንን የአጠቃቀም ደንብ (ውል) ሲጥሱ፣

•   በማጭበርበር ወይም በሕገ-ወጥ ድርጊት ላይ ከተሰማሩ፤

•   አገልግሎቱን ወይም ክሬዲቶችን አግባብ ባልሆነ መልኩ ከተጠቀሙ፤

•   ሲስተሞቻችን ወይም ሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ አደጋ የሚደቅኑ ከሆነ፣

አካውንትዎን ለመሰረዝ (ለማጥፋት) የሚያስችለውን ክፍል (ፊቸር) በመጠቀም በማንኛውም ጊዜ አካውንትዎን ማቋረጥ ይችላሉ።

10. መረጃ መሰረዝ

አካውንት ሲሰረዝ፡

•   በአገር ውስጥ  ያለ መረጃ ወዲያውኑ ይወገዳል።

•   በሰርቨር በኩል  ያለ የአካውንት መረጃ፣ በሕግ፣ በቁጥጥር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በደህንነት፣ ማጭበርበርን በመከላከል ወይም በፋይናንስ ግዴታዎች ምክንያት መረጃውን ማቆየት ካልተጠየቀ በስተቀር፣ የስረዛ ጥያቄው ተከታትሎ ከተፈጸመ በኋላ በተመጣጣኝ የጊዜ ገደብ ውስጥ ይሰረዛል ወይም ማንነቱ እንዳይታወቅ ይደረጋል።

ለሙሉ ዝርዝር መረጃ፣ የግላዊነት ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

11. የአእምሯዊ ንብረት መብት

ከ ethioCall ጋር የተያያዙ ሁሉም ይዘቶች፣ የንግድ ምልክቶች፣ ዲዛይን እና ኮድ  የቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ሚድል ኢስት ኤፍ.ዜ.ኢ  ንብረቶች ናቸው። ያለጽሑፍ ፈቃድ የመተግበሪያውን ማንኛውንም ክፍል መቅዳት፣ ማሻሻል ወይም ማሰራጨት አይችሉም።

12. የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች

አንዳንድ ባህሪያት በሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች (ለምሳሌ፡ አጓጓዦች፣ ጎግል፣ አፕል፣ ፌየርቤዝ) ላይ ይደገፋሉ። እኛ ለሚከተሉት ኃላፊነት አንወስድም፡

•   ለእነሱ መገኘት/አቅርቦት፤

•   ለአፈጻጸማቸው፤

•   በሶስተኛ ወገን ሥርዓቶች ምክንያት ለሚከሰቱ ማናቸውም ብልሽቶች።

12ሀ. የዋስትናዎች ማስተባበያ

ethioCall አገልግሎቱን የሚሰጠው "እንዳለ"  እና "እንዳለው የአቅርቦት ሁኔታ"  ላይ በመመሰረተ መልኩ በመሆኑ ግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ አገልግሎቱን በተመለከተ ዋስትና አይሰጥም፡፡

ሕጉ በሚፈቅደው ከፍተኛ ደረጃ፣ ስለ አገልግሎቱ ለገበያ የመቅረብ ብቃት፣ ለተወሰነ ዓላማ ተስማሚነት፣ መብትን አለመጣስ፣ መገኘት፣ ትክክለኛነት ወይም አስተማማኝነት ያሉ ማናቸውንም ዋስትናዎች በሙሉ እናስተባብላለን።

13. የኃላፊነት ገደብ

ሕጉ በሚፈቅደው ከፍተኛ ደረጃ፣ ethioCall ለሚከተሉት ኃላፊ አይሆንም፡

•   ለትርፍ ማጣት፤

•   ለመረጃ መጥፋት፤

•   ለአገልግሎት መቋረጦች፤

•   ቀጥተኛ ላልሆኑ ወይም ድንገተኛ ጉዳቶች፤

•   በኢንተርኔት አቅራቢዎ፣ በመሣሪያዎ ወይም በአገልግሎት ሰጪዎች (ኬሪየሮች) ምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች።

በዚህ ውል ውስጥ የተካተቱት ማናቸውም ነገሮች፣ ተፈጻሚነት ባለው ሕግ እንዲህ ዓይነቱ የኃላፊነት ገደብ በተከለከለበት ቦታ ላይ የኃላፊነት ገደብን አይጥሉም።

14. የውሉ ለውጦች

እኛ በማንኛውም ጊዜ ይህንን ውል ልናሻሽለው እንችላለን። መሠረታዊ ለውጦች በመተግበሪያው ወይም በድረ-ገጹ በኩል ይገለጻሉ። መተግበሪያውን መጠቀማቸውን መቀጠልዎ የተሻሻለውን ውል መቀበልዎን ያሳያል።

15. ገዢ ሕግ

ይህ ውል በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ሕጎች የሚመራ እና የሚተረጎም ይሆናል። የአገር ውስጥ ሕጎች ሌላ ነገር ካልጠየቁ በስተቀር፣ ማናቸውም ክርክሮች በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) ፍርድ ቤቶች የሚፈቱ ይሆናል።

16. የግንኙነት አድራሻ

ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ሚድል ኢስት ኤፍ.ዜ.ኢ

ቢሮ C1 – 1F – SF4499

አጅማን ፍሪ ዞን

አጅማን ዩናይት አረብ ኤምሬትስ

ኢሜይል፡ support@tsolution.ai

ድረ-ገጽ፡ www.tsolution.ai

መጨረሻ የተዘመነበት: 2026-06-16 13:23:06